በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ከተማ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 380 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወደመ
አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 27፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ከተማ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ግምቱ ከ380 ሺህ ብር በላይ በሆነ ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
እሳቱ የተነሳው በአንድ ግለሰብ ወፍጮ ቤት ከምሽት አንድ ስዓት ተኩል ገደማ መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ውበት መስፍን ለፋናብድካስቲንግ ኮርፓሬት ተናግረዋል።
በአደጋው ግምታቸው 382 ሺህ 150 ብር የሚያወጡ ንብረቶች ከመውደማቸው ባለፈ በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያልደረሰ መሆኑን ሀላፊው አያይዘው ገልጸዋል።
ከአደጋው በኃላ በስፍራው በተደረገ ቅኝት የመብራት ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ መጠነኛ መቆረጥ የታየ ሲሆን ትክክለኛው የአደጋ መነሻ እየተጣራ ነውም ተብሏል።
ሀላፈው አያይዘውም የእሳት አደጋው ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ በወቅቱ የአካባቢው ወጣቶች እና ማህበረሰቡ ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
በምናለ አየነው
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!