Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በሶስት አመታት እስከ 90 ሚሊየን ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ከ70 እስከ 90 ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ።

ለብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እስካሁን ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች ምዝገባ ማከናወናቸው ተገልጿል።

የብሄራዊ መታወቂያ በመላ ሀገሪቱ ዜጎች ማንኛውንም አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነም ነው የተነገረው።

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከፍተኛ ተቆጣጣሪ ቻሌ አምባዬ እንደገለጹት፤ የቀበሌ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ፣ ፓስፖርት፣ የልደት ካርድ፣ የትምህርት ማስረጃ፣ የባንክ አካውንት በመያዝ ብሄራዊ መታወቂያ ማውጣት ይቻላል።

በመሆኑም መረጃ ወደሚቀበሉት ማዕከላት በማቅናት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ጠቁመዋል።

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ ዳይሬክተር ሄኖክ ጥላሁን በበኩላቸው የብሄራዊ መታወቂያ ለዜጎች ዲጂታል በሆነ መንገድ ማንነታቸውን እንዲያረጋገጡ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ዲጂታል መታወቂያ እየተስፋፋ ለመጣው ዲጂታል አገልግሎት በር ከፋች እና ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።

የዲጂታል መታወቂያ ዘርፈ ብዙ ጠሜታ እንዳለው ጠቅሰው፤ ዜጎች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

በሲሳይ ዱላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.