Fana: At a Speed of Life!

3ኛው ዙር የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 859 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት ተመድቦለት ሲተገበር የነበረው የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ሶስተኛው ዙር ተጠናቀቀ፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (ዩ አይ አይ ዲ ፒ) የፌዴራል እና የክልል ስትሪንግ ኮሚቴ የጋራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ የከተሞች እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ መንግስት በከተሞች የሚታዩ ችግሮችን በመለየት መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም “ከተሞቻችንን የኢትዮጵያ ዕድገት ብልፅግና መነሻ ለማድረግ ማዕከል በመሆናቸው የተለምናቸውን ዕቅዶች ለማሳካት በጋራ መስራት ይገባል” ብለዋል፡፡

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ በበኩላቸው÷የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም በዋናነት በ117 ከተሞች እንደሚተገበር እና የባለድርሻ አካላትን ርብርብ እንደሚጠይቅ አስገንዝበዋል፡፡

በቤዛዊት ከበደ እና ቢንያም አስናቀ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.