ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመናኸሪያዎችን አገልግሎት አሰጣጥ ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመናኸሪያዎችን አገልግሎት አሰጣጥና የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ -19) ወረርሽኝን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ስራ ጎበኙ።
ዛሬ ማለዳ ላይም የአስኮ፣ የመርካቶና የአየር ጤና መናኸሪያዎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ተገልጋዮችን፣ ሹፌሮችና ሌሎችንም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ስርጭት ለመከላከል ስለሚያደርጉት ጥንቃቄና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ ማነጋገራቸውን ኢዜአ አገልግሎት ዘግቧል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በወጣዉ ድንጋጌ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።