የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል በያዝነው የመኸር ወቅት 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በዘር ለመሸፈን እየተሰራ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

August 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የመኸር ወቅት 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በተለያየ የሰብል ዘር ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

አቶ ሽመልስ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚሳካው በፍጥነት እና በጥራት ማምረት ሲቻል ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም የምርት አይነቶችን ለማብዛት እና ወደ ውጭ የምንልካቸውን ምርቶች ለመጨመር በተያዘው የመኸር ወቅት 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በተለያየ የሰብል ዘር ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በዚህ የመኸር ወቅትም÷ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በአዲስ የስንዴ ዘር ኢኒሼቲቭ ለመሸፈን እየሰራን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ለዚህ ስኬት ትልቅ ሚና እየተወጡ ለሚገኙ አርሶ አደሮችና የልማት ባለሙያዎችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!