Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የ2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷በዘንድሮው የ2015 የትመህርት ዘመን የ6 ክፍል ፈተናን በአጠቃላይ 73 ሺህ 667 ተማሪዎች ወስደዋል፡፡

ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 80 ነጥብ 2 ያህሉ 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ፈተናውን 50 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል እንደሚዘዋወሩም ጠቁመዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ÷ ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች በድጋሚ የሚማሩበት ሥርዓት መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል።

እንዲሁም ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ተዘዋውረው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች በዝውውር መመሪያ መሰረት እንደሚስተናገዱም ነው የተናገሩት።

የትምህርት ግብዓት ለማሟላት እየተደረገ ያለው ጥረት እንዲሁም መምህራንና የትምህርት አመራሮች ተማሪዎችን በማብቃታቸው ጥሩ ውጤት መመዝገቡን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ሀገሩን የሚወድ ጠንካራ ትውልድ ለመገንባት ና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.