በብሪታንያ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከአውሮፓ ከፍተኛው ሆኗል
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታንያ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከአውሮፓ ሃገራት ከፍተኛው ሆኗል።
በሃገሪቱ ቫይረሱ ከተከሰተ ወዲህ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከጣሊያን እና ስፔን በቁጥር በልጧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶሚኒክ ራብ በመላ ሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ 29 ሺህ 427 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።
ይህም ዓለም ላይ ከአሜሪካ ቀጥሎ ከፍተኛው ቁጥር ሲሆን፥ በአውሮፓ ደግሞ ቀዳሚው ሆኖ ተመዝግቧል።
በአሜሪካ በቫይረሱ ሳቢያ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።
በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፥ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል።
ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ነው የተባለው።
ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።