መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረት ልማት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር)÷ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አረጋግጠዋል፡፡
በዛሬው ዕለት የሚገቡትም ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሒደቱን ባቋረጠበት ዓመት ላይ ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎችን መሆናቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ግጭት ሳቢያ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሒደቱ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በመላኩ ገደፍ