Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያመጣውን ተጽዕኖ ከግምት በማስገባት የግብር ዕዳ ስረዛ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያመጣውን ተጽዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት ለግብር ከፋዮች የግብር ዕዳ ስረዛ አደረገ።

እዳው የተሰረዘላቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዚያ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ምህረት እንዲደረግላቸው መወሰኑን ተከትሎ ነው።

በዚህ መሰረት እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ እዳ ያለባቸው እንዲሁም ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም ሂሳባቸውን የሚዘጉ የውሳኔው ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ፍሬ ግብር፣ መቀጫ እና ወለድ ያለባቸው ተቋማት ዕዳ ሙሉ ለሙሉ መሰረዙም ነው የተገለጸው።

ከዚህ ባለፈም ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም ዕዳ ያለባቸው ተቋማት 25 በመቶ በአንድ ወር ለሚከፍሉ ወለድ እና እንደሚነሠሳላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም በአንድ ወር ሙሉ በሙሉ እዳቸውን ለሚከፍሉ ደግሞ 10 በመቶ ከፍሬ ግብሩ ተቀናሽ የሚደረግላቸው ሲሆን ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው የተባለው።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.