Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከመጭው ዓርብ ጀምሮ የሚኒባስ ተጠቃሚዎች የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአስገዳጅነት ሊጠቀሙ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከመጭው ዓርብ ጀምሮ የሚኒባስ ተጠቃሚዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ሊደረግ ነው።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን እንዳለው ተሳፋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጠቀም ሲንቀሳቀሱ ጭምብሎችን መጠቀም ይኖርባቸዋል።

ባለስልጣኑ ተሳፋሪዎች ያለ አፍ መሸፈኛ ጭምብል ታክሲ መጠቀም አይችሉም ብሏል።

የፐብሊክ ሰርቪስ ድርጅት ከዛሬ ጀምሮ ተሳፋሪዎች የአፍ መሸፈኛ ጭምብል በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ማስታወቁ ይታወሳል።

አፈጻጸሙን በተመለከተ ጣቢያችን በተለያዩ ስፍራዎች ባደረገው ቅኝት በርካቶች ያለ አፍ መሸፈኛ ጭምብል የትራንስፖርት አገልግሎት ሲጠቀሙ መታዘብ ችሏል።

መሰል ሁኔታዎች ህዝብ በሚበዛባቸውና በትራንስፖርት መስጫ ቦታዎች የህብረተሰቡን የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት ከፍ የሚያደርጉ ከመሆናቸው አንጻር ተገቢው ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።

በታሪክ አዱኛ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.