በአፋርና በጅቡቲ የሚገኙ የለይቶ ማቆያ ቦታዎች አሰራርና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ጉብኝት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፋርና በጅቡቲ የሚገኙ የለይቶ ማቆያ ቦታዎች አሰራርና በሂደቱ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ድጋፋዊ ምልከታ ተካሄደ::
በድጋፋዊ ምልከታው የሰላም ሚኒስቴር ፣የጤና ሚኒስቴር ፣የትራንስፖርት ሚኒስቴር ፣ የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ፣ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ፣ የአዲስ አበባ የለይቶ ማቆያ ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋ፡፡
የስራ ኃላፊዎቹመረ ሰመራ ዩኒቨርስቲ ተገኝተዉ ወደ ለይቶ ማቆያ የሚገቡ ሰዎች ከድንበር አንስቶ እስከ መቆያ ቦታዎች እስከሚገቡ ድረስና የኳራታይን አጠቃላይ ሁኔታውን በመገምገም ከሚመለከታቸው የግብረ ሀይል አባላት ጋር ተወያይተዋል።
ስራ ኃላፊዎች በጋላፊ ኬላ ተገኝተዉ የኮሮና ቫይረስን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ በድንበር አካባቢ የሹፈሮች ቅብብሎሽ ፣ በኬላዉ ከጅቡቲ አቋርጠዉ ወደ ሀገራችን የሚገቡ ሰዎች የሚስተናገዱበትን መንገድና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ቦታዉ ካሉ የጤና ባለሙያዎችና የፀጥታ አካላት ጋርም መክረዋል።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እና ሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችንና የፀጥታ አካላትን አበረታተው የበለጠ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸውም ጭምር ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ቡድኑ በቀጣይ ቀናት በድሬዳዋ ደወሌና በጊኒሌ ኬላዎች እንዲሁም በመስራቅ ሀረርጌ በመገኘት የለይቶ መቆያ አሰራር ቅኝት ያደረጋል ተብሏል ።