Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ከሮማኒያ አምባሳደር ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በኢትዮጵያ ከሮማኒያ አምባሳደር ሉሊያ ፓታኪ ጋር በጋራ ሊሰሯቸው በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

 

በውይይቱ ላይ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበሩ ታሪካዊ ግንኙነቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታው ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሙያተኞችን በማፍራት ለሃገር መከላከያ ያበረከተው አስተዋጽኦ ሰፋ ያለ መሆኑን ለአምባሳደሯ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

 

በዚህ ወቅት በጋራ ሊሰሩ በሚችሏቸው የትምህርትና የምርምር እንዲሁም የማማከርና የማኅበረሰብ ተኮር አገልግሎቶች ዙሪያም ከአምባሳደሯ ጋር ምክክር ተደርጓል።

 

የረጅምና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች፣ በአይ ቲ እና ሳይበር ደህንነት፣ በምርምር፣ በኦንላይን ላይብረሪ፣ እንዲሁም የአካዳሚክ ላቦራቶሪ መሰረተ ልማቶች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት መደረጉን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።

 

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብርጋዲየር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ፥ በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የተወሰኑና የተመረጡ የጋራ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

 

አምባሳደር ሉሊያ ከውይይቱ በኋላ የኢነጂነሪንግ ኮሌጅ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ፣ ኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ቤተ ሙከራዎች እና የኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ሰርቶ ማሳያን ጎብኝተዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.