የሀገር ውስጥ ዜና

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት የስያሜና ሎጎ ለውጥ አደረገ

By Mekoya Hailemariam

August 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት የስያሜና ሎጎ ለውጥ አደረገ።

የአዲስ ዋልታ አዲስ መንገድ የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ትናንት ተካሂዷል።

በዚሁ ስነስርዓት ላይ የሚዲያ ተቋሙ አዲሱን ዓርማ (ሎጎ) እና ስያሜ አስተዋውቋል።

በዚህም ተቋሙ ከዚህ በፊት በህዝብ ዘንድ የሚታወቀውን ስም “ዋልታ”ን አሁን ላይ ወደ “አዲስ ዋልታ” መቀየሩ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ የዜና፣ ፕሮግራም እንዲሁም ዶክመንተሪ ስራዎችን ለማስፋፋት ባለፉት ወራት የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ነው የተገለፀው።

በዚህ የማስተዋወቂያ መርኃ ግብር ላይ የአዲስ ዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ቦርድ አባላትን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና እንግዶች ተገኝተዋል፡፡