በሁለቱ ክልሎች ሕገ መንግስትና ሌሎች የሕግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልሎች ሕገ መንግስቶች እና በሌሎች የሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የክልል ማዕከል፣ የሁለቱም ክልሎች ዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡