Fana: At a Speed of Life!

የቆዳ ጤናን ለመጠበቅ ጠቃሚ ምክሮች

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ቆዳ በሰውነት ውስጥ ትልቁ አካል እንደመሆኑ መጠን ቆዳ የራሱ የሆኑ ትላልቅ ተግባራት አሉት።

የሙቀት መጠንን መቆጣጠር ፣ ጤናማ፣ ጠንካራ እና ንቁ ሆነው እንዲቀጥሉ ከበሽታ፣ ከኢንፌክሽን፣ ከፀሀይ እና ከሌሎች የከባቢ አየር ንጥረ ነገሮች እንደሚከላከልንን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በዚህም ቆዳ ብዙ ትኩረትን ይፈልጋል ስለሆነም የቆዳን ጤና ለመጠበቅ ከሚረዱ ነገሮች ውስጥ ደግሞ

-ሰንስክሪን በቋሚነት መጠቀም፡-ለፀሐይ ብርሃን ከመጋለጥዎ 30 ደቂቃዎች በፊት የፀሐይ መከላከያዎችን (ሰን ስክሪን) በቆዳዎ ላይ መቀባት ይመከራል።

ከቤት ውጭ ለረጅም ጊዜ ከቆዩ በየሁለት ሰዓቱ የጸሀይ መከላከያ መጠቀምን መዘንጋት የለበትም።

– ሴራማይድ እና አልፋ ሃይድሮክሲ ንጥረ ነገር ያላቸው ውህዶች (moisturizers)መጠቀም፡-እድሜ እየገፋ ሲሄድ በቆዳ ውስጥ ያሉት የዘይት እጢዎች እንቅስቃሴ እየቀነሰ ይሄዳል፣ ስለዚህም ቆዳ ይደርቃል፣ በቀላሉ ለቁጣ የተጋለጠ ይሆናል።

ከመታጠቢያ ከወጡ በኋላ በሶስት ደቂቃዎች ውስጥ እርጥበት መከላከያ መጠቀም ለቆዳዎ እንክብካቤ የሚከር ሲሆን÷ሴራማይድ ያላቸው ውህዶች ቆዳ በቀላሉ እርጥበቱን እንዳይለቅ እና እንዳይሰነጣጠቅ ይረዳናል።

– በቂ እንቅልፍ ማግኘት፡- በሚያሸልቡበት ጊዜ ሰውነትዎ በቆዳው ላይ የደም ፍሰትን ይጨምራል፣ ይህም ማለት ወደ ጤናማ ሁኔታ ይነሳሉ ማለት ነው።

– ሲጋራ እና መሰል የትንባሆ ውጤቶችን አለመጠቀም፡-ትንባሆ በቆዳ ሕዋሳት ላይ ውጥረት እና የደም ስሮች መጨናነቅን ሊያስከትል ይችላል።
የደም ስሮች ለቆዳችን ደም የሚያቀርቡባቸው ቦታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበቡ ይሄዳሉ፣ ይህም ለበለጠ መሸብሸብ፣ ያለጊዜው እርጅና እንደሚያስከትል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

-እንዲሁም በቂ ምግብ እና ውሃ መውሰድ የቆዳን ጤና ለመጠበቅ ከሚረዱ ነገሮች ውስጥ ይጠቀሳል፡፡

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.