የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል እርምጃዎችን ለመውሰድ ይገደዳል- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ

By Tibebu Kebede

May 07, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል ህገ መንግስቱን የሚጥሱ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ባስተላለፉት መልእክት፥ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጎልተው ከወጡ የህዝብ ፍላጎቶች አንዱ ህዝብ የሚሳተፍበትና የሚሰማበት የአስተዳደር ወይም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ፍላጎት ነው ብለዋል።