Fana: At a Speed of Life!

9ኛው የሕንድ-አፍሪካ አይ ሲ ቲ ኤክስፖ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠነኛው የሕንድ-አፍሪካ አይ ሲ ቲ ኤክስፖ ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ሁሪያ አሊ÷የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መሰንበት ሸንቁጤ በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ሽሪ ሮበርት ሼቲኪንቶንግ ጨምሮ የዘርፉ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ታድመዋል።

ኤክስፖውን የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከሕንዱ ቴሌኮም ኢኩዩፕመንት እና አገልግሎት ጋር በጋራ ያዘጋጁት ነው ተብሏል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ 30 የሕንድ አይ ሲ ቲ እና 16 የኢትዮጵያ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ኢዜአ ዘግቧል።

ኤክስፖ የአይ ሲ ቲ የስራ ፈጣሪዎችን ግዙፍ ኩባንያዎችን እንዲሁም የተለያዩ የቴክኖሎጂ ባለቤቶችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ መሆኑ ተመላክቷል።

እንዲሁም የኢትዮጵያን የ2025 የዲጂታል ስትራቴጂ ለባለድርሻ አካላት በማስተዋወቅ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለውም ተነስቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.