Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኮሮና ቫይረስ ከፐርል ሀርበር ጥቃት በከፋ አሜሪካን ክፉኛ እንደጎዳት ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮና ቫረስ ወረርሽኝ  ከፐርል ሀርበር እና  ከመስከረም አስራ አንዱ የሽብር ጥቃት በከፋ ሁኔታ አሜሪካን እንደጎዳት ገለፁ።

ፕሬዚዳንቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ጃፓን አሜሪካ ላይ ካደረሰችው የቦምብ ጥቃት እና ከሁለት አስርት አመታት በፊት ከደረሰው 9/11 ተብሎ ከሚጠራው የሽብር ጥቃት የከፋ ነው ብለዋል።

አሜሪካ እንዲህ ዓይነቱ ጥቃት ደርሶባት አያውቅም ነውያሉት ፕሬዚዳንቱ።

በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቻይና ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ቅድሚያ የወሰደችውን እርምጃ ኮንነዋል።

ቻይና በበኩሏ አሜሪካ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የምትሰጠው ምላሽ ትኩረት እንዳያገኝ በቻይና ለማሳበብ ነው ስትል ክሱን ውድቅ አድርገዋለች ።

በአሜሪካ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ73 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.