ቢዝነስ

ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የግብርና ምርቶች ከ850 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

By ዮሐንስ ደርበው

August 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ክትትል ከሚደረግባቸው ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የግብርና ምርቶች 854 ሚሊየን 834 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኘ፡፡

ለውጭ ገበያ የቀረቡት የግብርና ምርቶችም÷ የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ምርቶች፣ የብርዕና አገዳ ሰብሎች፣ የጫት ምርት፣ የቁም እንስሳት እና የደንና ደን ውጤቶች መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከሚቀርቡ የግብርና ምርቶች 1 ነጥብ 162 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኝት ታቅዶ እንደበር ተገልጿል፡፡

ማሳካት የተቻለውም የዕቅዱን 73 ነጥብ 58 በመቶ ብቻ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

የሰሊጥ ምርት የዓለም አቀፍ የገበያ ፍላጎትና ዋጋ መጨመሩ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚወሰድ ነው ብሏ ሚኒስቴሩ፡፡

ይሁን እንጅ ሰሊጥ በሚመረትባቸው አካባቢዎች በተስተዋለ የፀጥታ ችግር ምርቱ በወቅቱ ለገበያ ባለመቅረቡ በአፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፏል ነው የተባለው፡፡

የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ፣ የወጪ ምርቶችን ብዝኀነት ለማስፋት፣ የመዳረሻ ሀገራትን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም ገበያ እንዲተዋወቁ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች መከናወናቸውም ተጠቁሟል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!