Fana: At a Speed of Life!

በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከጃፓን የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከጃፓን ፓርላማ የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቤ ቶሺኬ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮችና በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ድጋፍ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ መክረዋል።

በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ÷በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይ ካ) ድጋፍና ትብብር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ውጤት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ከባቢ ያላትና አስቻይ አቅም እየገነባች መሆኑን ገልፀው÷ የጃፓን ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያስችሉ እድሎች ሰፊ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

አቤ ቶሺኬ(ዶ/ር) በበኩላቸው በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በተሰሩ ስራዎች በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው÷ ከአፈጻጸሞቹ ብዙ ልምድ መቅሰም እንደሚቻል አመልክተዋል።

በቀጣይም በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ያላቸውን የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ እንደሚጋብዙና እንደሚያበረታቱ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ለጋራ ውጤት የመስራት ፍላጎት እንዳላት ማረጋገጣቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.