የደም ማነስ ምልክቶች
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደም ማነስ በቂ ቀይ የደም ሴል ሳይኖር ሲቀር የሚከሰት የጤና እክል ነው።
የደም ማነስ የሚባለውም የሂሞግሎቢን መጠን ለወንዶች ከ13 ነጥብ 5 ግራም/ደሊ በታች እንዲሁም ለሴቶች ደግሞ ከ12 ግራም/ደሊ በታች ሆኖ ሲገኝ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ::
ለመሆኑ የደም ማነስ ምልክቶች ምንድናቸው?
ከደም ማነስ ምልክቶች ውስጥ የድካም ስሜት፣ ራስ ምታት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የቆዳ መገርጣት እና መድረቅ፣ የልብ ምት መጨመር፣ በታችኛው እግር ላይ ያልታሰበ እንቅስቃሴ ፣ቀዝቃዛ እጅ እና እግር፣ በአንዱ ወይም በሁለቱም ጆሮዎች ላይ ያልተለመደ ድምጽ ወይም ጩኸት እንደሚጠቀስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የደም ማነስ ካለብዎ የአይረን መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን እንደ የበሬ ሥጋ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ለውዝ፣ የወተት ተዋጽኦዎች፣ የፎሊክ አሲድ ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች እንደ ሎሚ እና ብርቱካንና ጥራጥሬዎች መመገብ ይመከራል::