በትግራይ ክልል አራት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መደበኛ የ24 ሰዓት እለታዊ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ ሚኒስቴሩ በደረሰው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል አራት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ በትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረጉ 85 የላብራቶሪ ምርመራዎች ውስጥ ነው አራቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው።
ይህንንም ተከትሎ ዛሬ ብቻ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባው ሰዎች ቁጥር 29 የደረሰ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 191 ደርሷል።