Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት ሹመት ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ፡፡

ሹመቱ የጸደቀው በውሳኔ ቁጥር 17/2015 በ1 ድምፅ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህ መሰረትም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ አባላት ፡-

1. አዝመራው አንዴሞ — ሰብሳቢ

2. ነጃት ግርማ (ዶ/ር) — ምክትል ሰብሳቢ

3. አቶ ሣዲቅ አደም — አባል

4. አቶ መስፍን እርካቤ — አባል

5. አብርሃም በርታ ዶ/ር) — አባል

6. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ተሾመ — አባል

7. አቶ ወንድሙ ግዛው — አባል

በመሆን የተሰየሙ ሲሆን÷ የቦርዱ አባላትም በጉባዔው ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.