Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፍ የሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፍ የሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ሙሃመድ ቢን አብደል ከሪም አል ኢሳ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሐይማኖት መቻቻል፣ በሰላም እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን÷ኢትዮጵያ በታሪኳ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ አውስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡ እንደ አል ነጃሺ መስጅድ፣ የሶፍ ዑመር ዋሻ እና ሌሎች ታሪካዊ መስጅዶች እና ሰነዶች መገኛ ሀገር መሆኗን  አስረድተዋል።

ዋና ጸሃፊው ሙሃመድ ቢን አብደል ከሪም አል ኢሳ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየውን የሃይማኖት መቻቻል እና በሰላም አብሮ የመኖር እሴት አድንቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.