Fana: At a Speed of Life!

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ የስራ ሃላፊዎች በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ነው የመከሩት፡፡

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ ፣የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ እና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ሃላፊዎችም ተሳትፈዋል፡፡

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ የስራ ሃላፊዎቹ በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.