Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከውጭ ሀገራት በየብስና በትራንዚት ወደ ክልሉ የሚገቡ የውጭ ተመላሾች  ለኮቪድ-19 መስፋፋት ስጋት መሆናቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠር ስራ ከውጭ ሀገራት በየብስና በትራንዚት ወደ ክልሉ የሚገቡት የውጭ ተመላሾች  ስጋት መሆናቸው ተገለፀ።

በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽና መልሶ ማቋቋም ባለሙያ አቶ ሀይሉ አያሌው እስከ ሚያዚያ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በክልሉ ከውጭ ለተመለሱና ንክኪ ላላቸው 942 ሰዎች ምርመራ እንደተደረገላቸውና ሰባት ሰዎች እንደተገኘባቸው አመለክተዋል።

ከእነዚህም መካከልም አምስቱ ማገገማቸውንና ሁለቱ ህክምናቸውን በመከታተል ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ለአንድ ሚሊዮን 36 ሺህ 12 ቤቶች ቤት ለቤት ልየታ የተሰራላቸው ሲሆን፥ በልየታው የተለያዩ የመተንፈሻ አካል ችግር የተገኘባቸው 569 ሰዎች መገኘታቸውን ከእነዚህም መካከል 510 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ሁሉም ነፃ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

በክልሉ ለኮቪድ 19 የበለጠ ተጋላጭ የሆኑት አካባቢዎችን በተመለከተም በየብስ ክልሉ ከአፋር ክልልና ከጅቡቲ በሚዋሰንባቸው በኦሮሚያ ልዩ ዞን (ባቲ)፣ በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ እንዲሁም ክልሉ ከሱዳን በሚዋሰንበት ምዕራብ ጎንደር ሲሆኑ በአየር ደግሞ ከውጭ ሀገራት በትራንዚት ወደ ክልሉ የሚገቡት የውጭ ተመላሾች የሚገኙባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ባለሙያው በህብረተሰቡ ዘንድ መዘናጋት በመኖሩ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ይህ በማይቻልበት ሁኔታ ደግሞ ጭምብል መጠቀም ተገቢ መሆኑንና ከውጭ ተመላሾችም እንደገቡ በስልክ ቁጥር 6981 ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.