Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከዓለም ሙስሊም ሊግ ዋና ፀኃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የዓለም ሙስሊም ሊግ ዋና ፀኃፊ ሙሓመድ ቢን አብዱልከሪም አል-ዒሳን (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ።

 

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በተለይም ከአረብ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል።

 

ዋና ፀሐፊው ሙሐመድ ቢን አብዱልከሪም አል-ዒሳ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

 

በውይይቱም የኃይማኖት መቻቻልንና ሰላምን ጨምሮ በጋራ ፍላጎቶች በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

 

አቶ ደመቀ በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ያላትን ቦታ አንስተዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.