Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በመስኖ ልማት የስንዴ ምርታማነትን ለመጨመር መታቀዱን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስንዴን ከውጭ በማስገባት ፈንታ በመስኖ በማልማት ምርታማነት ለመጨመር መታቀዱን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛውን የስንዴ መጠን ለማምረት ከሚችሉ ሀገራት መካከል መሆኗን አስታውቀዋል።

የስንዴ ምርት አሁን ከውጭ ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ በቅርቡ ተስፋ የሚጣልባቸው ውጤቶች መታየታቸውን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም በሶማሌ ክልል ያለው የቆላ ስንዴ ምርት የሚያበረታታ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አያይዘውም ለዓመታዊው የአረንጓዴ ዐሻራ የሚሆን ችግኝ በሦስቱም ክልሎች በሚገባ እየተዘጋጀ መሆኑን መገንዘባቸውንም አውስተዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.