ስፓርት

በአለም ዋንጫው እንግሊዝ ለፍፃሜ ደርሳለች

By Mikias Ayele

August 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች አለም ዋንጫ እንግሊዝ አስተናጋጇን አውስትራሊያን 3 ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ ደርሳለች፡፡

ለእንግሊዝ ኤላ ቶኒ፣ ላውረን ሄምፕ እና አሌሲያ ሩሶ ጎሎችን ሲያስቆጥሩ የአውስትራሊያን ብቸኛ ጎል ሳም ኬር አስቆጥራለች፡፡

የእንግሊዝ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከ1966 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍፃሜ መድረስ የቻለ ሲሆን ሴት አምበሶቹ በመጭው እሁድ ከስፔን አቻቸው ጋር ለፍፃሜ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡