ባለስልጣኑ በአራት የግንባታ ዘርፎች ከ50 ሺህ በላይ ፈቃድ ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመትበአራት ዋና ዋና የግንባታ ፈቃድ ዘርፎች 50 ሺህ 569 ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡
በባለስልጣኑ የግንባታ ፈቃድ ዳይሬክተር ደሳለኝ አብዲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ 16 ሺህ 757 የአዳዲስ ግንባታ፣ 3 ሺህ 125 የማሻሻያና ማራዘሚያ እንዲሁም 30 ሺህ 687 የዕድሳት ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
ከተሰጡ ፈቃዶችም 55 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ71 ሚሊየን 850 ሺህ ብር በላይ መሰብሰቡን ጠቁመው÷ ከዕቅዱ አንጻር ከፍተኛ ገቢ የተገኘው የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ማሻሻያ በመደረጉ ነው ብለዋል፡፡
የተሰጠው ፈቃድ እና የተገኘው ገቢ በማዕከሉ የግንባታ ፈቃድ ዘርፍ ብቻ የተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በባለስልጣኑ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ከማል ጀማል (ኢ/ር) እንዳሉት÷ በተደረገ ክትትል ሕግ በተላለፉ 1 ሺህ 119 አልሚዎች ላይ እንደየጥፋታቸው የተለያየ እርምጃ ተወስዷል፡፡
ከዚህም ከ23 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!