Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የምታከናውነውን ስራ ሀገራት ሊደግፉ ይገባል – ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ የምታከናውነውን ስራ የበለጸጉ ሀገራት በፋይናንስ መደገፍ አለባቸው ሲሉ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የኢንዱስትሪና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኮፕ-28 ፕሬዚዳንት ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢር ገለጹ።

19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ “የአፍሪካን የአካባቢ ችግሮች ለመፍታት ዕድሎችን መጠቀም ትብብርን ማጎልበት” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የኢንዱስትሪና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኮፕ-28 ፕሬዚዳንት ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢር በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ዓለምን ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል።

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቀነስ በሚደረገው ሂደት የፋይናንስ አቅርቦት፣ ተደራሽነትና ተመጣጣኝነት መጓደል ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነም ገልጸዋል።

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሰ የሚገኘውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ደግሞ ጠንካራ የትብብር ሥርዓት በመዘርጋት ውጤታማ ስራ ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡

ከሰባት በመቶ በታች የአፍሪካ የበካይ ጋዝ ልቀት ድርሻ ከሰባት በመቶ በታች ቢሆንም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ገፈት ቀማሽ መሆኗ ግን አይቀሬ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የበለጸጉ ሀገራት የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት እውን ለማድረግ የአህጉሪቱን የታዳሽ ኃይል ልማት በገንዘብ መደገፍ ይኖርባቸዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.