ስፓርት

ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁበት የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል

By ዮሐንስ ደርበው

August 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍጻሜ ውድድር ምሽት 1፡25 ላይ ይካሄዳል፡፡

በውድድሩ÷ አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ይስማው ድሉ ተጠባቂ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ቀን 12፡05 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ሂሩት መሸሻ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ኃየሎም ተጠባቂ ናቸው፡፡

ትናንት በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ÷ አትሌት ሂሩት መሸሻ 1ኛ፣ ድርቤ ወልተጂ 2ኛ እንዲሁም ብርቄ ኃየሎም 3ኛ ከየምድባቸው በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸው ይታወቃል፡፡

19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሀንጋሪ ቡዳፔስት በመካሄድ ላይ ነው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!