ጠ/ሚ ዐቢይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በስልክ ተወያዩ።
በውይይታቸው የኮቪድ19 ወረርሽኝን መከላከል በሚቻልባቸው አግባቦች ዙሪያ መምከራቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኮቪድ19 ያስከተላቸውን ፈተናዎች ለመከላከል እየወሰዱት ያለው እርምጃ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
አያይዘውም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምላሽ ዕቅዱ አምስት ምሰሶዎች ኢትዮጵያ ከለየቻቸው ተቀዳሚ ተግባራት ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውንም አንስተዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።