ስፓርት

ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ በ1 ሺህ 500 ሜትር ለፍፃሜ አለፉ

By Feven Bishaw

August 20, 2023

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌት ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወደ ፍፃሜ አለፉ፡፡

አትሌት ብርቄ ኃየሎም ርቀቱን በ4 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ ከ46 ማይክሮ ሰከንድ 2ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ማለፏን ስታረጋግጥ በተመሳሳይ ከምድብ ሁለት ድርቤ ወልተጂም 3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ18 ማይክሮ ሰከንድ በመግባትና 2ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ማለፍ ችላለች ፡፡

አትሌት ሂሩት መሸሻ 9ኛ በመውጣት ወደሚቀጥለው ዙር ማለፍ አልቻለችም፡፡