Fana: At a Speed of Life!

ትኩረት በሚሹ ተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ የሚመክር የአፍሪካ ሀገራት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቆላማና ሐሩራማ አካባቢዎች ትኩረት በሚሹ ተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ የሚመክር የአፍሪካ ሀገራት ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ጉባኤው የጤና ሚኒስቴር፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ትራኮማና ዓለም አቀፍ ቆላማና ሀሩራማ አካባቢዎች ተላላፊ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት ነው።

በጉባኤው ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ ዓለም አቀፍ ቆላማና ሐሩራማ አካባቢዎች ተላላፊ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ተሾመ ገብሬና ኢትዮጵያን ጨምሮ የ13 የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስቴር እና የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ትራኮማና ሌሎች ትኩረት የሚሹ ተላላፊ በሽታዎች በምስራቅና ደቡባዊ የአፍሪካ አገራት ተጽዕኖ እያሳደሩ እንደሚገኝ ዶክተር ተሾመ ገልጸዋል።

ተላላፊ በሽታዎቹን ለመከላከል የጋራ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቴክኖሎጂና ፈጠራ በመታገዝ በሽታዎችን ለመከላከል እየተደረጉ ባሉ ጥረቶችና በመጡ ለውጦች ዙሪያ ከተለያዩ ኀገራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.