ስፓርት

ኢትዮጵያ የምትካፈልባቸው 2 የፍጻሜ ውድድሮች ምሽት ላይ ይካሄዳሉ

By ዮሐንስ ደርበው

August 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምትካፈልባቸው የሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር እና የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሠናክል የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ምሽት ላይ ይካሄዳሉ፡፡

ምሽት 4፡31 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ ይጠበቃሉ፡፡

እንዲሁም ምሽት 4፡42 ላይ በሚካሄደው የወንዶች 3 ሺህ ሜትር የመሠናክል ፍፃሜ ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ ተጠባቂ ናቸው፡፡

በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ የሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!