Fana: At a Speed of Life!

በቂ ውሃ የመጠጣት የጤና በረከቶች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ ጤናማ ሰው በቀን ውስጥ 8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት እንዳለበት በዘርፉ የተጠኑ በርካታ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

በቂና ንጹህ ውሃ መጠጣት ንጥረ ምግቦችን ወደ ሴሎች ለማጓጓዝ፣ ቆሻሻን ለማስወገድ፣ የሰውነት መገጣጠሚያዎችን እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

ንጹህና በቂ ውሃ መጠጣት በርካታ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ያህል፦

1. የቆዳ ጤንነትን ለመጠበቅ፦ በቂ የሆነ ውሃ መጠጣት ቆዳችን ጠንካራና ጤናማ እንዲሁም ለስላሳ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

2. የአንጎል ተግባራን ለማሳለጥ፦ በቂ የሆነ ውሃ ያለመጠጣት በአንጎል ተግባራት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል።

3. የሰውነት ሙቀት መጠንን ለመቆጣጠር ይረዳል፦ በቂ ውሃ በሰውነታችን ውስጥ ከፍተኛ የላብ ክምችት እንዲፈጠር በማድረግ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ኬሚካሎችን በላብ መልክ እንዲወገዱ ከማድረጉም በላይ የሰውነታችንን ሙቀት ለመቆጣጠርም ይጠቅማል፡፡

4. በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል፦ ንጹህ ውሃ አዘውትሮ መጠጣት በየትኛውም ከባድ ህመም የመጠቃት እድልን ይቀንሳል

5. የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል፦ ምግብ ከተመገብን በኋላ በቂ ውሃ መጠጣት ጥሩ የምግብ ልመትና መንሸራሸር እንዲፈጠር በማድረግ የምግብ የመፈጨት ሂደቱ ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

6. የደም ዝውውር ስርዓትን ያሻሽላል፦ በየቀኑ በቂ ውሃ ስንጠጣ በደም ዝውውር ስርዓታችን ላይ በርካታ አዎንታዊ ለውጦች ስለሚፈጠሩ እንደ ደም ግፊት፣ የልብ ድካም፣ ስትሮክ አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ ያደርጋል፡፡

7. መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል፦ መጥፎ የአፍ ጠረን በአብዛኛው ጊዜ የሚከሰተው ውሃን አዘውትሮ ባለመጠጣት ሲሆን በአፋችን ውስጥ የሚፈጠሩ ባክቴሪያዎች በቀላሉ እንዲራቡ እድልም ይፈጥራል፡፡

8. ክብደት ለመቀነስ ያግዛል፦ አዘውትሮ ውሃ መጠጣት ክብደት ከመቀነሻ ዘዴዎች አንዱ ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያት ውሃ የሜታቦሊክ እንቅስቃሴን ከፍ ስለሚደርግ ነው፡፡ ይህም የምናቃጥለውን የካሎሪ መጠን ከፍ እንዲል በማድረግ ክብደት እንድቀንስ ያስችላል፡፡

9. ድርቀትን ይከላከላል፦ በቂ ውሃ መጠጣት ለድርቀትን የሚከላከል ሲሆን በድርቀት ከተጋለጥንም ከህመሙ እንድናገግም ያስችለናል፡፡

10. የኩላሊት ጠጠርን ለማሰወገድ ይረዳል፦ ከፍ ያለ ፈሳሽ መውሰድ በኩላሊቶች ውስጥ የሚያልፈውን የሽንት መጠን እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን ይህም ጠጠሩ እንዲወገድ ያግዛል፡፡

ምንጭ፦ኸልዝ ላይን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.