ኮቪድ -19 በዩናይትድ ስቴትስ የስራ አጦች ቁጥር በከፋ ሁኔታ እንዲያሻቅብ አድርጓል
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ሀገሪቱ በበርካታ አስርት ዓመታት ውስጥ አይታው የማታውቀው የስራ አጥ ቁጥር እንዲኖራት አድርጓል።
ሀገሪቱ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ብላ እንቅስቃሴን በመገደቧ ብቻ ስራቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ተመልክቷል።
በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር ላይ ብቻ 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች ስራቸውን አጥተዋል።
የሀገሪቱ የሰራተኞች ስታትስቲክስ ቢሮ እንዳለው የሀገሪቱ ያለፈው ወር የስራ አጥ ቁጥር 14 ነጥብ 7 በመቶ ደርሷል።
እስከፈረንጆቹ ግንቦት 2 ድረስ 33 ነጥብ 5 ሚሊየን አሜሪካውያን ስራ አጥ መሆናቸውን በማሳወቅ በዚህ ምክንያት የሚገኝ ክፍያን ለመቀበል ተመዝግበዋል።
ስራቸውን ካጡት ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ በመዝናኛ ኢንዱስትሪ፣ በምግብና መጠጥ አቅርቦት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ናቸው ተብሏል።