Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በኢንቨስትመንት ዘርፍ እየተሳተፉ ላሉ አርሶ አደሮችና አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በኢንቨስትመንት ዘርፍ እየተሳተፉ ላሉ ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችና አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት እውቅና ተሰጠ።

የእውቅና ስነስርዓቱ በጅማ ከተማ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ከጅማ፣ ቡኖ በደሌና ኢሉ አባቦራ ዞኖች በቡና፣ በእህልና በሻይ ልማት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ተሳትፈውታል።

ከዚህም በተጨማሪ በጅማ ከተማ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅተው ውጤታማ የሆኑ ወጣቶች በስነስርዓቱ ላይ ተሳትፈዋል።

አርሶ አደሮቹና ወጣቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ከመሆን አልፈው በኢንቨስትመንት ዘርፍ እያበረከቱ ላለው አስተዋጽኦ የኢንቨሰትመንት ፈቃድና የእውቅና የምስክር ወረቀት በኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተበርክቶላቸዋል።

ስነስርዓቱን በንግግር የከፈቱት የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መኪዩ መሀመድ ግንባር ቀደም አርሶ አደሮቹና ወጣቶቹ ለስኬታቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላልፏል።

የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር አቶ ዋሲሁን ጎልጋ በኦሮሚያ ክልል በአጠቃላይ ለ 1 ሺህ 666 አርሶ አደሮች እውቅናና የኢንቨስትመንት ፍቃድ እንደሚሰጥ በመግለፅ አርሶ አደሮቹና ወጣቶቹ ለሌሎች ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ሀገሪቷ የጀመረችውን ልማት ለማሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያዱርጉ ጥሪ አስተላልፏል።

በሙክታር ጠሀ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.