Fana: At a Speed of Life!

ማይክ ፖምፔዮ በቀጣዩ ሳምንት እስራኤልን ሊጎበኙ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ በቀጣዩ ሳምንት እስራኤልን ሊጎበኙ ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የዌስት ባንክ የተወሰኑ ክፍሎችን ለመያዝ በሚያደርጉት ጥረት ዙሪያ ላይ ያተኮረ ውይይት ለማድረግ ያለመ ነው።

በጉብኝታቸውም ከኔታንያሁ ጋር የጥምር መንግስት ለመመስረት ከተስማሙት ቤኒ ጋንትዝ ጋርም ይመክራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ከዚህ ባለፈም አሜሪካ እና እስራኤል ኮቪድ19ኝን ለመከላከል በሚያደርጉት ጥረትና በቀጠናዊ የደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

ጉብኝቱ የፊታችን ረቡዕ ለአንድ ቀን እንደሚካሄድም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.