የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል አንፃር ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በከተማዋ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመገኘት ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል አንፃር ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ነው ሚንስትሯ የተናገሩት ።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንዲሁም በተጓዳኝ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም ቡድኑ ጎብኝቷል።