Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የግብርናና የትምህርት ሚኒስቴሮች ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የግብርና ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ አደረጉ።

በሀገሪቱ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ተከትሎ በቀረበው ጥሪ መሰረት በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የግብርና ሚኒስቴር ደግሞ 1 ሺህ ኩንታል ስንዴ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ የትምህርት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ለሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃግብር የሚያግዝ ዘመናዊ ኢንዱስትሪያል ስቶቭ ድጋፍ አድርጓል።

ከተቋሞቹ የተደረገውን ድጋፍ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ እንዳወቅ አብጤ እና የአዲስ አበባ የብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር በጋራ በመሆን ተቀብለዋል።

ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተቋማቱ ባደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው በተለይ የትምህርት ሚኒስቴር ያደረገው ዘመናዊ ኢንዱስትሪያል ስቶቭ ለትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃ ግብር በእጅጉ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

የግብርና ሚኒስቴርም ከዚህ ድጋፍ በተጨማሪ አስተዳደሩ በቅርቡ ተግባራዊ ላደረገው የከተማ ግብርና ዘርፍ አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ላይ መሆኑን ኢንጅነር ታከለ ኡማ ማናገራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.