Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በድምሩ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 2 ሺህ 481 አርሶና አርብቶ አደሮች ወደ ኢንቨስተርነት ተሸጋገሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል 2 ሺህ 481 አርሶ እና አርብቶ አደሮች ወደ ኢንቨስተርነት ተሸጋገሩ።

የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት በሰበታ አርሶ እና አርብቶ አደሮቹን ወደ ኢንቨስተርነት የማሸጋገር ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በስነስርአቱ ርእሰ መስተዳደሩ አቶ ሽመልስ፥ መንግስት የአርሶ እና አርብቶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ ይሰራል ብለዋል።

በግብርና ላይ እየተሰራ ላለው ሰፊ ስራ ሽግግሩ በጣም አስፈላጊ መሆኑ መሆኑ ተመልክቷል።

እውቅናውን ያገኙት አርሶ እና አርብቶ አደሮች ግንባር ቀደም ሆነው በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ልማት እና በግብርና ሜካናይዜሽን ዘርፍ ላይ ተሰማርተው ከ77 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥረው የቆዩ ናቸው።

አርሶ እና አርብቶ አደሮች ዛሬ ወደ ኢንቨስተርነት ለመሸጋገር የበቁት አርሶ አደር መሆናቸው የተረጋገጠ፣ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ያፈሩ፣ ለቀጣይ ስራ የቢዝነስ ፕላን ያዘጋጁ፣ ካላቸው ሀብት 20 በመቶ መቆጠብ የቻሉ ከኪራይና ከሊዝ ክፍያ ነፃ የሆኑ ናቸው።

አርሶ እና አርብቶ አደሮቹ በድምሩ ከ10 ቢሊየን በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ መሆናቸውም በስነስርአቱ ተጠቅሷል።

አርሶ እና አርብቶ አደሮቹ በአምስት ክላስተሮች ማለትም በጅማ፣ ሰበታ፣ ነቀምቴ፣ ሻሸመኔ፣ እና አዳማ በተካሄዱ ስነስርአቶች ነው እውቅና የተሰጣቸው።

ኢንቨስተሮቹም ክልሉ የኢንቨስትመንት ባለው በዚሁ ሳምንት የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.