ስፓርት

በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር እና የ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ማጣሪያ ሁሉም አትሌቶች ለፍጻሜ ደረሱ

By ዮሐንስ ደርበው

August 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሽቱን በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር እና 3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሠናክል የማጣሪያ ውድድር የተሳተፉ ሰባት አትሌቶች ወደ ፍጻሜ አልፈዋል፡፡

በተደረገው የ5 ሺህ ሜትር የማጣሪያ ውድድር÷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 2ኛ እንዲሁም አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ከየምድባቸው ማጠናቀቃቸውን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 4ኛ እና አትሌት መዲና ኢሳ 6ኛ ደረጃን ይዘው ከየምድባቸው በማጠናቀቃቸው ነው ለፍጻሜ የደረሱት፡፡

በተመሳሳይ ምሽቱን በተካሄደ የ3 ሺህ ሜትር የሴቶች የመሠናክል ማጣሪያ ውድድር ሁሉም ተወዳዳሪዎች ማለትም÷ አትሌት ሎሚ ሙለታ፣ አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ወደ ቀጣዩ የውድድር መርሐ ግብር አልፈዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!