የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ክልል አቀፍ የውይይት መድረክ በቡታጅራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው::
አቶ እንዳሻው ትናንት ምሽት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዜና መጽሔት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአጭር ጊዜ ወደ ስራ ለማስገባት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ክልሉን ፈጥኖ ወደ ስራ ለማስገባትም ዛሬ የ100 ቀን እቅድ ቀርቦ በአመራሩ ምክክር እንደሚደረግበት ጠቁመዋል፡፡
ሰላምን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ የጠቀሱት አቶ እንዳሻው÷ በየአካባቢው ያሉ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ከህዝቡ ጋር የመጀመሪያ ዙር ውይይት ይደረጋል ነው ያሉት።
የክልሉ ህዝብ ከክልሉ መንግስት ጋር ተቀራርቦ እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወጣቶቹን በተለያዩ ዘርፎች በማሳተፍ የልማት ሀይል በማድረግ እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡
በሲሳይ ዱላ