Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት አቋርጠው የነበሩ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ናቸው-ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በ2013 ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 24 ሺህ ተማሪዎችን በመቀበልና በማስተማር ላይ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ(ዶ/ር) ÷ ከ2013 ሰኔ 21 ቀን ጀምሮ በክልሉ በነበረው ግጭት ምክንያት የከፍተኛ ትምህርት ተቋርጦ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዚህም በወቅቱ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ ከነበሩ 46 ሺህ ተማሪዎች መካከል 22 ሺህ የሚሆኑትን በሀገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲማሩ በማደረግ ከፊሉ መመረቃቸውን ተናግረዋል።

የተወሰኑ ተማሪዎችም በተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ላይ እንደሚገኙም ነው የጠቀሱት።

በጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሰሜኑ ጦርነት በውይይት በመፈታቱ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ስራ ለማስገባት የዝግጅት ስራዎች ሲደረጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በ2013 ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 24 ሺህ ተማሪዎችን በመቀበልና በማስተማር ላይ መሆናቸውን ሰለሞን(ዶ/ር) ገልጸዋል።

ከዩኒቨሲቲዎቹ መካከል ሙሉ ለሙሉ ተማሪዎቻቸውን የተቀበሉ እንዳሉ ጠቅሰው፤ መቀሌ ዩኒቨርሲቲም በ2013 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ሲሆን በቀጣይ ሌሎችንም ለመቀበል ተዘጋጅቷል ብለዋል።

መምህራንና ተማሪዎችም የስነ-ልቦና ማገገሚያ ስልጠናዎች እንዲያገኙ፣ ተከታታይ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ አዳዲስ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም ካላቸውም በቀጣይ የሚወሰን ይሆናል ነው ያሉት።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.