Fana: At a Speed of Life!

በበርካታ መስኮች ከቻይና ጋር ስምምነት መደረጉ ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዕዳ ክፍያ የእፎይታ ጊዜ ማግኘትን ጨምሮ በበርካታ መስኮች ከቻይና ጋር ስምምነት መደረጉ ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ።

በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የብሪክስ ጉባዔ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የሚቀጥለው ዓመት ዕዳ ክፍያ አጠቃላይ የዕዳ ማሸጋሸግ ሥራው እስከሚከናወን ድረስ ቻይና ለኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት የእፎይታ ጊዜ መስጠቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም በበርካታ መስኮች የትብብር ስምምነት ማድረጋቸውን ገልጸው፥ ይህም በጣም ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ባደረጉት ምክክር÷ በሣይንስና ቴክኖሎጂ፣ ወታደራዊ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት መስኮች ለመሥራት መስማማታቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

እነዚህ ሁሉ ትብብሮች የኢትዮጵያን ትልቅነት እና ተደማጭነት የሚያሳዩ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.