Fana: At a Speed of Life!

ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 1፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት አምስት ቀናት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና በንግድ ማጭበርበር  ከ40 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ  ዕቃዎች በቁጥጥር ስር  መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከሚያዝያ 26 እስከ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ከተያዙት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ የተለያዩ የጥይት ዓይነቶችና ጦር መሳርያዎች፣ ተሽከርካሽሪዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ጥራታቸው ያልተረጋገጡ የተለያዩ ዓይነቶች ምግብና የምግብ ነክ ዕቃዎች፣ ቅሽር ቡና፣ አዳዲስና አሮጌ አልባሳት እንዲሁም ሲጋራ ይገኙበታል ተብሏል።

ከዚያም ባለፈ በገቢ ዕቃ አወጣጥ ቅጣትና  ታክስ ሳይከፈል ሊጭበረበርሩ የነበሩ የተለያዩ የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ዕቃዎች መያዛቸው ተገልጿል።

ህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ጅግጅጋ፣ ሞያሌ፣ ድሬደዋ፣ ሀረር፣ ሞጆ፣ አዲስ አበባ፣ አዋሽ እና ሌሎች የጉምሩክ ኬላ ጣቢያዎች የተያዙ መሆናቸውን ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.