Fana: At a Speed of Life!

ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ለመፍታት ፓን አፍሪካኒዝም ወሳኝ ነው – አምባሳደር ጀማል በከር

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ለመፍታት ፓን አፍሪካኒዝም ወሳኝ ነው ሲሉ በፓኪስታን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር ተናገሩ፡፡

አምባሳደሩ በፓኪስታን ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ አምባሳደር ጀማል በከር÷ ፓን አፍሪካኒዝምን ማስፋፋት በአሁን ሰአት እየተከሰቱ ያሉ እንደ አየር ንብረት ለውጥ፣ ሽብርተኝነት፣ ስደት እና የአለምን ኢኮኖሚ ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል።

አምባሳደር ጀማል የመላ አፍሪካን መርሆዎች በጋራ በማቀፍ የአፍሪካን የጋራ ጥቅሞች በአለም አቀፍ መድረክ ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በኢስላማባድ የአፍሪካ ሚሲዮን ዲን እና የሞሮኮ አምባሳደር መሃመድ ካርሙኔም÷ የአፍሪካ ሀገራት የአህጉሪቱን ብሎም የአለምን ጉዳዮች ለመፍታት ያላቸውን አንድነት አድንቀዋል።

አምባሳደሩ የመላ አፍሪካን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ ፓን አፍሪካኒዝምን ለማስተዋወቅ እርምጃዎችን እንደሚወስዱም አፅንዖት ሰጥተዋል።

በተመሳሳይም በውይይቱ የተገኙት የአፍሪካ ሀገራት የሚሲዮን መሪዎች  የአፍሪካን አንድነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸው ለጋራ ጥቅሞች ተቀራርበው ለመስራት መስማማት ላይ ደርሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.