Fana: At a Speed of Life!

የአለርጂ መከላከያ መንገዶች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አለርጂ በምግቦች፣ ብናኞች፣ የአየር ሁኔታ እና ሌሎች ነገሮች ምክንያት ሊመጣ ይችላል፡፡

ንጥረ ነገሩ ወይም ለሰውነትዎ የማይስማማ ነገሮች ላይ የበሽታ መከላከል ስርዓትዎ የሚሰጠው ምላሽ በሰውነትዎ ላይ አለርጂን ያስከትላል፡፡

በዚህም እብጠት፣ ማስነጠስ ወይም ሌሎች የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን ፥ እንደግለሰቡ የአለርጂ ዓይነትና ሁኔታ ምላሹ የተለያየ እንደሚሆንም ነው የሚገለጸው፡፡

አለርጂ እንዴት ይታከማል?

አለርጂን ጨርሶ ማጥፋት እንደማይቻል ይነገራል፤ መከላከል ግን ይቻላል፤ በብዙ የህክምና ባለሙያዎች የሚመከረው አለርጂ ከሚያስከትሉብዎ ነገሮች መራቅ ለነገ የማይባል መፍትሄ ነው፡፡

ሆኖም ይህን አማራጭ መውሰድ የማይችሉበት ሁኔታ ከሆኑ የህክምና አማራጮችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

ይህም ከህክምና ባለሙያ ጋር በመነጋገር የመድኃኒት አማራጭን መጠቀም ይቻላል፤ የህክምና ባለሙያን ሳያማክሩ መድኃኒት መውሰድ ግን አይመከርም፡፡

በተጨማሪም ከሃኪምዎ ጋር በመመካከር በቤት ውስጥ ሊታከም የሚችሉበትን መንገድ መፈለግ ሌላው አማራጭ ነው፡፡
ይህን የቤት ውስጥ ህክምና ከማድረግዎ በፊት በቤትዎ ውስጥ የሚያዘጋጁት ንጥረ ነገር ሌላ አለርጂ ላለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አለብዎ፡፡

ብዙዎች አለርጂ ጉንፋን ከሚመስል ማስነጠስ፣ የቆዳ ችግርና ሌሎች ለከፋ ጉዳት የማያስከትሉ ጉዳቶች ቢኖሩትም ፥ በአንዳንድ ሰዎች ለህይወት አስጊ ሊሆንም ይችላል፡፡

እንደአብነትም የምላስ እና የአፍ እብጠት፣ የልብ ምት መጨመር፣ የመተንፈስ ችግር፣ ራስን መሳትና ሌሎች ከፍ ያሉ ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡

በዚህም አለርጂው ከፍ ያሉ ጉዳቶችን የሚያስከትልብዎ ከሆነ ምንጊዜም ጥንቃቄ ሊለይዎት አይገባም፡፡ ከዚህ ካለፈም የድንገተኛ ህክምና ዘዴዎችን ከሃኪምዎ ጋር ቢወያዩበት ሲል ኽልዝላይን ይመክራል ፡፡

#Alergy #Health #Treatment

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.